[ Log In ]
Page: 1


Project Documents
የፕሮጀክት: ቅ/ያሬድ መንፈሳዊ ት/ቤት የተማሪዎች መኝታ ቁሳቁስ ማሟያ
ጠቅላላ ወጪ:  $7,551.00
የፕሮጀክቱ ዓይነት: የአብነት ት/ቤቶች
የሚጀመርበት ቀን: 05-01-2016
የሚጠናቀቅበት ቀን: 09-30-2017
ሀገረ ስብከት: ማዕከላዊ ትግራይ

One Time Donation (አንዴ ብቻ የሚሰጥ)
Amount(USD):
PayPal. The safer, easier way to pay/አስተማማኝ ፤ ቀላል የመክፈያ መንገድ::
 
 
Monthly Donation (በየወሩ የሚሰጥ)
Amount(USD):
PayPal. The safer, easier way to pay/አስተማማኝ ፤ ቀላል የመክፈያ መንገድ::
 
 

የፕሮጀክት ዝርዝር: የፕሮጀክቱ ማረጋገጫና አስፈላጊነት፡ የቅደስ ያሬድ መንፈሳዊ ት/ቤት በአሁኑ ወቅት ከንባብ፣ ቅዳሴ፣ ሰዓታት ጀምሮ ቅኔ፣ አቋቋም፣ ድጓ፣ ዝማሬ-መዋስዕት፣ የትርጓሜ መጻሕፍት ከ20 በላይ በሚሆኑ መምህራን እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በአብነት ት/ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎችም ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ሲሆን ከ 88 በላይ በአዳሪነት እንዲሁም በተመላላሽ የሚማሩትን ጨምሮ ከ 150 በላይ ተማሪዎች በተለያየ ጉባኤያት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ የርዕሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ያሬድ መንፈሳዊ ት/ቤት ሕንፃ በ 1954 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ አርቆ አሳቢነት በዘመናዊ መልክ ተገንብቶ የተደራጀ ነበር፡፡ ከጊዜ ብዛት የውስጥ ቁሳቁሱን መተካት ባለመቻሉ ተማሪዎች ባጋጠማቸው የመኝታና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ባዶ ወለል ላይ በመተኛታቸው በጤና ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ሆኗል። ከዚህም በተጨማሪ የተማሪዎቹ ማደሪያ ክፍሎች ከአያያዝ ጉድለትና ተፋፍጎ ከመኖር የተነሣ ለበሽታ አምጪ ሕዋሳት መራቢያ ሆኗል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የውስጥ ክፍሎች እድሳት እና የመኝታ ቁሳቁስ እና አልባሳት እገዛ ፕሮጀክት መተግበር አስፈላጊ ሆኗል፡፡ የፕሮጀክት ይዘት፡- ፕሮጀክቱ የአብነት ትምህርት ቤት እድሳት፣ ለ88 ተማሪዎች የመኝታ ቁሳቁስ ማለትም፡- ተደራራቢ አልጋ፣ ብርድልብስ፣ አንሶላና የመሳሰሉትን ማሟላት ይገኝበታል። የፕሮጀክቱ በጀት፡- የአብነት ትምህርት ቤቱ እድሳትና የመኝታ ቁሳቁስ ጠቅላላ በጀት ብር 351,216.00 ሲሆን የመኝታ ቁሳቁስ ግዥ ለመፈጸም በማኅበረ ቅዱሳን የካናዳ ማዕከል በኩል 160 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ቀሪው ($7,551) ከበጎ አድራጊዎች የሚጠበቅ ነው፡፡

የፕሮጀክት ተጠቃሚ መረጃ
ስም: ርዕሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ቅደስ ያሬድ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት
አድራሻ: ማዕከላዊ ትግራይ
የፕሮጀክት አስተባባሪ
ስም:  ማኅበረ ቅዱሳን/Mahibere Kidusan
የአስተባባሪ:  Kesis Girma Kasa Masresha
ስልክ:  (240) 593-8040
ኢሜይል:  us.monasteries@eotcmk.org
ዜና ገዳማት/Gedamat News

Project Videos